free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

አሏህ ሙስሊም ብሎ በደነገገለት መጠሪያ ልቡ ያረካችለት ሙስሊም ማን አለ? ያ ኡመተ ሙሐመድ! በሃይማኖታችሁ ጉዳይ ቡድንተኝነትን እና ቲፎዞ ፈላጊነትን ተጠንቀቁ!!!


PicsArt 1262319362772 1

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


free book gift

በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)

እኛ ሙስሊሞች በዲነል ኢስላም አስተምህሮት ስንኖር መዋደድ ፣ መተነነስ ፣ ሰላም ፣ መቻቻል ፣ ወንድማማችነት እና አንድነት የሚሉ እሴቶችን ተላብሰን መሆን አለበት። ምክኒያቱም እነዚህ ነገሮች የነዛ ብርቅየ ሶሃቦች ማንነት ፣ የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮት ውጤቶች ሲሆኑ ልዑል ሃያል የሆነው አምላካችን አሏህ ወደ አንድነት እና ወደ ወንድማማችነት ጎዳና እንድንመጣና በነዚህ እሴቶች እንድንኖር ያስገድደናልና ነው።

አሏሁ አዘወጀል በቅዱስ ቃሉ በሱረቱል ኢምራን አንቀፅ 103 ላይ እንዲህ ይለናል፦

=<({አል-ቁርአን 3:103})>=

{103} ሁላችሁም በአሏህ ገመድ ተሳሰሩ፤ አትከፋፈሉም። እርስ በርስ ጠላቶች በነበራችሁ ጊዜ አሏህ በእናንተ ላይ የዋለውን ውለታ አስታውሱ ልቦቻችሁን አስተሳሰረ። እናም በችሮታው ወንድማማቾች ሆናችሁ። በእሳት ጉድጎድ አፋፍ ላይ በነበራችሁም ጊዜ ከሷም ጠበቃችሁ። እናም ትመሩ ዘንድ አሏህ አንቀፆቹን ግልፅ አደረገላችሁ።


ከላይ በተጠቀሰው የቁርአን አንቀፅ አሏህ(ሱ.ወ.ተ) በአሏህ ገመድ ማለትም በቁርአን እና በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሱና ተሳሰሩ ካለ ብኋላ መከፋፈልን ወይም ቡድንተኝነትን እና ቲፎዞ ፈላጊነትን ሐራም ማድረጉን እንረዳለን።

ይሁንእንጅ አንዳንድ እራሳቸውን እንደ ሙወሂድ ሌሎችን ልክ እንደ ሙሽሪክ እና እንደ ቢድእይ የሚመለከቱ ሰዎች ወደ አንድነት የሚጣሩትን ሰዎች ጥሪያቸው ከተውሂድ ውጭ እንደሆነ በማስመሰል ይህ ኡማ አንድ ሊሆን የሚችለው በተውሂድ ብቻ ነው ሲሉ ይስተዋላል።

እንደ ሚታወቀው የኢስላም መሰረቱ ንፁህ የሆነ የጠራ አሃዳዊነት ነው። ያለ አሃዳዊነት ኢስላምም ሆነ አንድነት ይኖራ ብሎ ማሰብ ቂልነት ነው። ሆኖም ወደ አንድነት ስንጣራ ከካፊሮች ጋር ወይም ከሙሽሪኮች ጋር አንድ እንሁን እያልን አይደለም። በዚህም መንገድ ወደ አንድነት የሚጠራ አይኖርም! የእኛ በክፋት የተሞላ አዕምሮ አስተሳሰብ ወጤት ካልሆነ በቀር።

ይልቁንም አንድነት ስንል በመዝሃብ አስተምህሮቶች ያሉ ልዩነቶችን ፣ የዳዕዋ ያካሄድ ልዩነት እና በኡለማዎች መካከል ያለውን ሂላፍ እንዲሁም አንዳንድ ጥቃቅን የሉይነት ሃሳቦችን ወደጎን በመተው አንድ ወደሚያደርገን ቁርአን እና ሱና እንመለስ፤ አሏህ ለኛ ከደነገገልን መጠሪያ ውጭ ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ስም አንለጥፍ ነው እየተባለ ያለው።

አምላካችን አሏህ በሱረቱል ኒሳዕ አንቀፅ 59 ላይ እንዲህ ይለናል፦


=<({አል-ቁርአን 4:59})>=

{59} እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን እና መልዕክተኛውን ታዘዙ፤ እነዚያ በስልጣን ላይ ያሉትንም ታዘዙ። በሆነነገር ብትለያዩ በአሏህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደሆነ ወደ አሏህና ወደ መልዕክተኛው መልሱት። ያም የተሻለና ለመጨረሻ ውሳኔ የቀረበ ነው።


እነዛ ብርቅየ ሶሃቦች የደረሱበትን ልዩ የሆነ ጊዜ አናስታውስ፤ ኸሊፋዎች የነበሩበትንም ዘመን አናስታውስ! ለዛ ታላቅነት እና ግርማሞገስ ያበቃቸው አንድነታቸው እንደሆነ እንረዳለን። በዚህ ዘመን ያለን የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ኡመቶች ግን እየተከፋፈልን እና የሉዩነት አመለካከቶችን እያሰፋን በመምጣታችን ፣ በመካከላችን ፍቅርና መተሳሰብ በመጥፋቱ ምክኒያት ጠላቶቻችን ከሚያጠቁን በላይ እኛው በኛው ላይ ጠላቶች ሁነን አንዳችን የአንዳችነን ደም እያፋሰስን ፣ ለስልጣንና ለጥቅም ብለን ወንድሞቻችነን እያሳሰርን እራሳችነን ለውድቀት እና ለውርደት አጋልጠናል። እጆቻችነም በጥፋት ላይ ሆነው በሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ ዘመተዋል። በዚህም ምክኒያት ምድር ላይ ያለው ፈሳድ በረከተ!


=<({አል-ቁርአን 6:159})>=

{159} እነዚያ የካዱ አንዳቸው ላንዳቸው ረዳቶች ናቸው። እናም እናንተ ይህን የማተደርጉ ከሆነ በምድር ላይ ፊትና እና ትልቅ ፈሳድ ይኖራል።


እንደሚታወቀው የሉይነት ሃሳቦች የተነሱት ዛሬ ብቻ አይደለም በነዛ ብርቅየ ሶሃቦች ዘመን የልዩነት ሃሳቦች ነበሩ። ሆኖም ግን ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ያስማሟቸና ወደ አንድነት ጎዳና ያመጧቸው ስለነበር አንድነታቸው እንጅ ልዩነታቸው ጎልቶ አይታይም። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ከሞቱ ቡኋላም የመጀመሪያው ኸሊፋ ማን መሆን አለበት በሚለው ጉዳይ ተለያይተው የነበረ ቢሆንም አቡ በክር(ረ.ዐ) የመጀመሪያው ኸሊፋ በሆኑ ጊዜ ችግሩ በሰላም ተፈታ። የሙስሊሞችም አንድነት ሶስተኛው ኸሊፋ ኡስማን(ረ.ዐ) እስኪገደል ድረስ ቀጠለ። እሱ በተገደለ ጊዜ ሙስሊሞች በፓለቲካዊ ጉዳይ ተለያዩ። ይሁን እንጅ በሸሪአዊና በአምልኮት ጉዳይ ልዩነት አልነበራቸውም።

እንዲሁም በአራቱ የመዝሃብ ባለቤቶች መካከል ልዩነት የነበራቸው ቢሆንም እነዚህ የመዝሃብ ባለቤቶች አንድኛው ሌላውን አይኮንንም፤ ከመስርመም አያስወጣም ነበር። ዛሬ የነዚህ መዝሃብ ተከታዮች ልዩነቱን እስፍተውት አንዱ እንዱን መኮነኛና ከመስመር ማስወጫ መሳሪ አድርገውት ይገኛል። ልክ ሰለፍይ ነን ባዮች በተውሂድና በቢድአ ሽፋን ኡለማዎችን እና ዱአቶችን አደባባይ ላይ እንደ ሚኮንኑትና ከመስመር እንደሚያስወጡት ሁሉ ማለት ነው።

አምላካችን አሏህ በሱረቱል ሑጅራት አንቀፅ 10 ላይ እንዲህ ይለናል፦


=<({አል-ቁርአን 49:10})>=

{10} አማኞች ወንድማማቾች ናቸው። በመካከላቸውም እርቅን ፍጠሩ፤ ምህረትም ታገኙ ዘንድ አሏህን ፍሩ።

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) አትጠላሉ ፣ አትቀናኑም አንዳችሁ ባንዳችሁ ላይ ጀርባውን አይስጥ! የአሏህ ባሪያዎች ሆናችሁ ወንድማማቾች ሁኑ ብለዋል።


ሆኖም ዛሬ ሰለፍይ ነን ባዮች ቢድእይ ያልሆኑ ኡለማዎችን እና ዱአቶችን አደባባይ ላይ የሚያወግዙበትን በቢድእይነት የሚፈርጁበትን እና የነሱን አመለካከት ስላልደገፍ ወይም ደግሞ እራሳቸውን ሰለፍይ ብለው ስላልጠሩ ብቻ ከመስመር የሚያስወጡበትን አጋጣሚ እየተመለከትን ነው። እንዲሁም አንዳንድ ሱፍዮች አንድ ሰው ሙስሊም የመሆኑ እና ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የመውደዱ መገለጫው ተሰባስቦ ጫት እየቃመ ሰለዋት በማድረግና በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ውዴታ ስም በመጨፈር ይመስል ይህን ያላደረገ ሰው ረሱልን እንደማይወድ በማሰብ ይህንን ሰው ከመስመር ሲያስወጡት ይታያል።

ታዲያ ይህ አካሄድ ጠማማ አካሄድ ከመሆኑም በላይ ተውሂድ በሚል ሽፍን እና የረሱል ውዴታ በሚል የጫት ሙቀት እና ጭፈራ የስሜት መፈክር እንግበው ጭፍንና ጠባብ አስተሳሰባቸውን በማራመድ ለሰዎችም ሆነ ለራሳቸው ስም እየለጠፍ ከየትኛው ጀመዓነህ? በሚል የብድንተኝነት ጥሪ ኡማውን እየከፋፈሉት ይገኛሉ።

አሏህም ይህን አይነት ተግባራችነን ሲገስፅ በሱረቱል አንአም አንቀፅ 159 ላይ እና በሱረቱል ኢምራን አንቀፅ 105 ላይ እንዲህ ይለናል፦


=<({አልቁርአን 6:159})>=

{159} በእርግጥም ሃይማኖታቸውን የከፋፈሉ (በሃይማኖታቸው ቡድንተኝነትን ያበጁ)፤ ከነሱ ምንም ጉዳይ የለህም፤ ጉዳያቸው ከአሏህ ጋር ነው። ከዚያም ይስሩት የነበረው ነገር ሁሉ ይነገራቸዋል።

=<({አለቁርአን 3:105})>=

{105} ግልፅ ማስረጃ ከመጣላቸው ቡኋላ እንደ ተከፋፈሉትና እንደተለያዩት አትሁኑ! በእርግጥ እነዚያ እነርሱ ታላቅ ቅጣት አላቸው።


=<({አልቁርአን 6:159})>=

{159} በእርግጥም ሃይማኖታቸውን የከፋፈሉ (በሃይማኖታቸው ቡድንተኝነትን ያበጁ)፤ ከነሱ ምንም ጉዳይ የለህም፤ ጉዳያቸው ከአሏህ ጋር ነው። ከዚያም ይስሩት የነበረው ነገር ሁሉ ይነገራቸዋል።

=<({አለቁርአን 3:105})>=

{105} ግልፅ ማስረጃ ከመጣላቸው ቡኋላ እንደ ተከፋፈሉትና እንደተለያዩት አትሁኑ! በእርግጥ እነዚያ እነርሱ ታላቅ ቅጣት አላቸው።


አሁንም አንድነት ሲባል አንዳንድ ሰዎች ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ኡመቴ በ73 ቡድን ይከፋፈላሉ። ከነዚህም መካከል አንዷ ብቻ ናት የጀነት ብለዋል! ታዲያ ይህን ሐዲስ ልታስወግዱት ነው ወይስ ይህን ሐዲስ አትቀበሉትም ሲሉ ሽንጣቸውን ገትረው ፅልመት በወረሰው አስተሳሰባቸው ሊሞግቱ ይሞክራሉ።

አዎ! ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ኡመቴ በ73 ቡድን ይከፋፈላሉ ብለዋል። በእርግጥም ቡድንተኝነትን እና ቲፎዞ ፈላጊነትን እየተመለከትን ነው። እዚህ ላይ ልናስተውለው እና ልብ ልንለው የሚገባ ነገር ቢኖር ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ኡመቴ በ73 ቡድን ይከፋፈላሉ አሉ እንጂ ተከፋፈሉ አላሉም። ከዚህ በተቃራኒው አሏሁ አዘወጀል በብዙ የቁርአን አያዎች ስለ አንድነት እና ስለ ወንድማናችነት አስተምሮናል። እንዲሁም የአሏህ መልዕክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) ስለ አንድነት እና ስለ ወንድማማችነት በቡዙ ሐዲሶች አስተምረውናል። ሶሃባዎችም በተግባር ኑረው አሳይተውናል።

ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በብዙ ሐዲሶች ወደ አንድነት እና ወደ ወንድማማችነት ሲጠሩን ሙስሊም ለሙስሊም ልክ እንደ ጡብ ነው እንድኛው ሌላኛውን ያጠነክረዋል፤ ሙስሊም ለሙስሊም ልክ እንደ አንድ አካል ነው አንዱ የአካል ክፍል ሲታመም ሙሉ አካል ይታመማል፤ የአሏህ ባሮች እንደሆናችሁ ወንድማማቾች ሁኑ፤ አንዳችሁም አላመናችሁም ለራሱ የወደደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ እያሉ ነበር እኛን ሊገባን በሚችሉ ምርጥ ምሳሌዎች ያስተማሩን።

አንድ ሰው በቡድንተኝነት የተጠመዱ ሰዎችን ረሱል ምን ነበሩ ሱፍይ ፣ ወሃብይ ፣ ሰለፍይ ፣ ኸዋሪጅ ነበሩ? ብሎ ቢጠይቃቸው መልሳቸው ሙስሊም ነበሩ የሚል ነው። እሽ ሰለፍይ የሚያስበለው የሰለፎችን መንገድ መከተል ከሆነ ሰለፎችን ብንከተልም ከዛ በላይ የአሏህ መልዕክተኛ አሉና ለምን ሙሐመዳን ተብለን አንጠራም? አልሃምዱ ሊላህ ከዚህም በላይ አሏህ ሙስሊም የሚል መጠሪያ በቅዱስ ቃሉ ደንግጎልናል። እኛ ለራሳችን ከምናስበው በላይ አሏህ ስለኛ ያውቃልና ሙስሊም የሚለው መጠሪያችን ደንግጎልናል።

አሏሁ አዘወጀል በሱረቱል ኢምራን አንቀፅ 102 ላይ እና በሱረቱል ፉሲለት አንቀፅ 33 ላይ እንዲህ ይለናል፦


=<({አል-ቁርአን 3:102})>=

{102} እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህ ሊፈራ እንደሚገባው ፍሩት። እናም ሙስሊም ሆናችሁ እንጅ እንዳትሞቱ።

=<({አል-ቁርአን 41:33})>=

{33} ወደ አሏህ ከጠራና መልካምም ከሰራ፤ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለ ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን አለ?


እናም ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ ፈትዋ ለመስጠት አንቻኮል፤ በፌስቡክ ፣ በዋትሳፕ ወይም በሌሎች ማህበራዊ ድህረገፆች ላይ ያምናገኛቸውን ሰዎች ሁሉ ፈትዋ አንጠይቅ! በዚህ ዘመን ለኡመታችን ትልቅ ፈተና ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነውና። እራሳችነንም ለክፍፍል ምቹ አናድርግ (ምቹ ሁኔታ አንፍጠር)፤ ሂወታችንን በቁርአን እና በሐዲስ ብቻ እንምራ! ማንም ሰው ሱፊያ ፣ ወሐቢያ ፣ ሰለፊይ ፣ ተክፊሪ ፣ ኸዋሪጅ ከነዚህ መካከል የትኛው ነህ? ብሎ ቢጠይቅህ መልስህ !እኔ ሙስሊም ነኝ! ብቻ ይሁን!!!

ሰባት ሰማያትን እና ምድርን አስተናብሮ የፈጠረው አሏሁ አዘወጀል የሰጠኝ ስም በቂየ ነው። ቲፎዞና አጨብጫቢ ፈላጊዎች ከዚህ የተለየ ስም እንዲሰጡኝ ፈፅሞ አልፈልግም!!! አሏህ በመጨረሻው መለኮታዊ ራዕዩ የደነገገልኝ መጠሪያየ ልቤን አርክቶታልና!!!!


To get free Islamic pamphlets, brochures and books delivery please subscribe to Youth Mission የወጣቱ ተልዕኮ

© የወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)

Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ

page:
http://facebook.com/youth.mission29

Blog
http://youth-Mission.blogspot.in?m=1

website:
http://youth-mission.mobie.in

'~'-.,__,.-'~'
_,.-'~''~'-.,_

2708

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ


XtGem Forum catalog